በቃላችን መሰረት የትም ያተነዱ 00 የሆኑ መኪኖችን ተደራሽ ለአባላቱ አስረክቧል።
March 11, 2026
ተደራሽ ከበላይ አብ ሞተርስ ጋር ባደረገው ስምምነት 50 መኪኖችን ተረክባል። በዛሬው እለትም ናሚ 01 2024 ሞዴል የኤሌክትሪክ መኪናን 25% ለቆጥቡ እና ስድስት ወር ለሞላቸው አባላቱ ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ቁልፋቸውን አስረክቧል። ፕሮግራሙም እጅግ በደመቀ መልኩ የተከናወነ ሲሆን የተደራሽ ቁጠባና ብድር ዋና ስራ አስኪያጅና እና የበላይ አብ ሞተርስ ሀላፊዎች ተገኝተው ከተደራሽ አባላትና ከሚዲያ ባለሙያዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰተዋል። የመኪና ባለቤቶችም በቴክኒክ ሀላፊዎች ስለ መኪናው ገለፃ ከተደረገላቸው የመኪና ቁልፋቸውንም ተረክበዋል።