Loading…

በኬንያ የሚገኘው የኒው ፎርቲስ ሳኮ ከፍተኛ ማኔጅመንቶች እና የቦርድ አመራሮች በተደራሽ ቤት ጉብኝት አደረጉ።

March 23, 2026

የጉብኝቱ ዋነኛ አላማ ተደራሽ የሚሰጠውን አገልግሎቶች ፣ የሚጠቀበውን ሲስተም እና የሚያከናውናቸውን ተግባራት ጠቅለል ባለ መልኩ ለማወቅ እና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያሰበ ነው። እንግዶቹን በመቀበል የእንኳን ደህና መጣቹ መልእክት ያስተላለፉት የተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ታመነ ናቸው።መባስከተልም በዋና ስራ አስኪያጁ በኩል ስለተደራሽ አምሰራረት ስለተጓዘበት መንገድ እና ስለስኬቱቸሁ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡በመቀጠልም የሲስተም ክፍል ዋና ሃላፊ በሆኑት በአቶ ኦዳ ጋዲሳ ለእንግዶቹ ተደራሽ አሁን ላይ እየተጠቀመበት ስለሚገኘው ኮር ባንኪንግ ሲስተም ሰፊ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡ ሀላፊው አክለውም በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ያለው ሲስተም ለአባላት የተሻለ አገልገሎት ለመስጠት ከማስቻሉ ባለፈ ምን ያህል ችግር ፈቺ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የተደራሽ ከወልድ ነፃ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በድሩ ጀማል ተደራሽ የሸሪያ ህጉን በጠበቀ መልኩ ለአባላቱ ከወለድ ነፃ የሆነ የፋይናስ አገልግሎት በምን መልኩ እየሰጠ እንደሚገኝ ለእንግዶቹ አብራርተዋል፡፡በልዑካን ቡድኑ በኩል ተደራሽ በሚጠቀመው ሲስተም ዙሪያ እና በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ጥያቄ የተነሳ ሲሆን በሃላፊው በኩል ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡
እንግዶቹም ተደራሽን በመጎበኘታቸው እና ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው ተደራሽ ስላደረገላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ በማመስገን የሀገናቸው ባህላዊ ልብስ በስጦታ ምልክ አበርክተዋል ፡፡

Tederash Assistant

Always Online