Loading…

ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ በጅማ ከተማ የሚገኘው ቅርንጫፉን በይፋ አስመረቀ ፡፡

March 31, 2026

ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ በመጋቢት 19/ 2018 በጅማ ከተማ በመገኘት ቅርጫፉን በይፋ አስመረቀ፡፡
በምረቃ ስነስርአቱ ላይም በዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አለማየሁ ታመነ በኩል ስለህብረት ስራ መርህ፣ ስለ ተደራሽ አመሰራረት ስለተከናወኑ ተግባራት እና ሊሰሩ ስለታቀዱ ስራዎች ገለፃ ተደርጓል፡፡ በመረሃ ግብሩ ላይ ለአባላቱ በህብረት ስረ ማህበሩ ስር እንዴት መንቀሳቀስ እንደሚቻል እና በምን መልኩ የፋይናስ አቅምን ማጠናከር እንደሚቻል ሰፊ ገለፃ ተደርጎበታል፡፡
በስልጠናው ላይ የጅማ ከተማ ስራ እና እድል ፈጠራ ሃላፊ አቶ ሀይደር አባመንጫ፣የጅማ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ዘርፍ ሃለፊ ፈቀደ ታመነ ፣ኮማንደር ታከለ ለቺሳ የቀድሞ የጅማ ዞን አጠቃላይ የፖሊስ አዛዣ፣ አባገዳዎች፣የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተደራሽ ነባር እና አዲስ አባላት ተገኝተዋል፡፡
መርሃ ግብሩ በአባገዳዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ዋና ስራ እኪያጅ ስለህብረት ስራ መርህ፣ ስለ ተደራሽ አመሰራረት ስለተከናወኑ ተግባራት እና ጅማን ጨምሮ በሁሉም የተደራሽ ቅርጫፎች ሊሰሩ ስለታቀዱ ስራዎች ገለፃ አድርገዋለዋል፡፡ በተጨማሪም ህብረት ስራ ማህበራት ለህብረተሰቡ አስተማማኝ የፋይናስ ምሰሶ በመሆን ረገድ ያላቸውን ሚና እንዲሁም በህብረት በጓዝ እነደሚቻል በሰፊው አስረድተዋል፡፡
የጅማ ከተማ ስራ እና እድል ፈጠራ ሃላፊ አቶ ሀይደር አባመንጫ ተደራሽ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበው እድገት እና ስኬት ቀላል የማይባል እንደሆነ ተናግረው በዚህም ስኬት አባላት ሊኮሩ እንደሚገባ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ህብረት ስራ ማህበራት የማህበረሰብን እድገት በማረጋገጥ በኩል እና አስተማማኝ የሆነ የፋይናስ አቅርቦት እንዲኖር ከማስቻል አንፃር የሚኖራቸው አስተዋፆ ቀላል የሚባል እንዳልሆነም አክለው ገልፀዋል፡፡ ነባር እና አዲስ አባላት በተደራሽ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያላቸውን ጥያቄዎች ለዋና ስራ አስኪያጁ ያነሱ ሲሆን ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡

Tederash Assistant

Always Online