ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ በዛሬው ዕለት አዲስ ቅጥር ለፈፀሙ ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ፡፡
April 20, 2026
ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ በዛሬው ዕለት አዲስ ቅጥር ለፈፀሙሰራተኞች ስልጠና ሰጠ፡፡
ተደራሽ በቅርቡ ህብረት ስራ ማህበሩን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሰራተኖች አቅም ግንባታ ያተኮረ ስልጠና አራት ኪሎ በሚገኘው ዋና ስልጠና ሰጠ፡
ስልጠናውን የሰጡት ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ታመነ ናቸው፡፡ ስልጠናው በአገልግሎት አሰጣጥ ፣ በስራ ስነምግባር፣በአቅም ግንባታ እና በብድር አሰራርላይ ያተኮረ ነው፡፡ ተደራሽ የሚያቀርበውን አገልግሎትን ፈልጎ የመጣን ደንበኛ በምን መልኩ ማስተናገድ እንደሚገባ ሰፊ ገለፃ ከተካሄደበት በኀላ ከሰራተኞች ጋር ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ብድር ፈልጎ ወደ ህብረት ስራ ማህበሩ የመጣን ተገልጋይ ብድር ከማበደር ባለፈ ብድሩ በተባለለት አላማ ላይ መዋሉን መከታተል እንደሚያስፈልግ አፅኖት ተሰቶበታል፡፡
የተሸለ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለደንበኞች ለማቅረብ ስለተቋሙ ጠንቅቆ ማወቅ አስፈላጊ መሆኑ የተነሳ ሲሆን የማኔጅመነት ድጋፍ እና ቁርጠኝነት ለተሸለ ስራ ወሳኝ መሆኑም ተገልፃል፡፡
በማስከተልም ሙያዊ ስነምግባር ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ሰራተኞች ሊላበሱት ስለሚገባ ሙያዊ ስነምግባር አቶ አለማየሁ በዝርዝር አስረደተዋል፡፡
የሙያ ስነምግባር መላበስ ለስኬት ያላውን ሚና በተገቢው መልኩ ያስረዱት ዋና ስራ አስኪያጁ ስነምግባር የተላበሰ ሰራተኛ ደንበኛን ለማርካት እና የተሸለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችለው ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው በነገው እለትም ቀጥሎ የሚውል ይሆናል፡፡