Loading…

ኮሚሽኑ ድጋፍ ላደረጉ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በዛሬው ዕለት እውቅና አበረከቱ ተደራሽ ሚዲያና ኮምኒኬሽን

March 11, 2026

የኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር "ኅብረት ሥራ: ከምርት እስከ ግብይት፣ ከአምራች እስከ ሸማች" በሚል መሪ ቃል ከጥር 25 - 30/2018 ዓ.ም በጋራ ባዘጋጁት ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም ድጋፍ ላደረጉ ኅብረት ሥራ ማኅበራት በዛሬው ዕለት ልዩ የምስጋና መረሐግብር በማዘጋጀት እውቅና ተሰቷል፡፡

በምስጋና መርሐግብሩም ላይ ይህ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም አንዲሳካ የበኩላቸውን ለተወጡ የተለያዩ የህብረት ስራ ማህበራት በዋና ኮሚሽነሩ ጌትነት ታደሰ እና መምክትል ኮሚሽነሩ ሺሰማ ገ/ስላሴ አማካኝነት የእውቅና ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ላበረከተው አስተዋፆ ከኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ከሆኑት ከአቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ የእውቅና ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡
የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ በእውቅና እና ሽልማት በመርሐግብሩ ላይ የምስጋና መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ድጋፍ ያደረጉት ማኅበራት የኮሚሽኑ የምንግዜም አጋር መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽነሩ አክለውም፣ ዘንድሮ በተከናወኑት መርሐግብሮች የተገኘውን የገንዘብ ድጋፍ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ በመጠቀም የተረፈውን ብር በኮሚሽኑ የህፃናት ማቆያ ግንባታ ላይ ማዋል እንደተቻለ የጠቆሙ ሲሆን ለዚህም ድጋፍ ያደረጉ ማኅበራትን ከልብ አመስግነዋል፡፡

Tederash Assistant

Always Online