July 27, 2026
ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ከወለድ ነፃ የፋይናስ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እና ሌሎች የተደራሽ ውስጣዊ አሰራሮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ፡፡ ይህን ለሁት ቀናት የቆየውን ስልጠና የተካፈሉት በዋና ቢሮ እንዲሁም በቅርጫፍ የሚገኙ የተደራሽ አዲስ እና ነባር ሃላፊዎች ናቸው ፡፡ስልጠናው ሃላፊዎችን እና ሰራተኞችን በማብቃት ለአባላት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ነው፡፡ በስልጠናው በስፋት ተደራሽ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች እና ያለውን አገልግሎት በምን መልኩ ለአባላት ባቅረብ እንደሚገባ ፣ስለቁጠባና ብድር አያያዝ ፣ስለውስጣዊ አሰራሮች እንዲሁም ፣ከወለድ ነፃ የፋይናስ አሰራር ላይ ሰፊ ገለፃ ተደርጎበታል፡፡ በስልጠናው የመጀመሪያ ቀን ላይ የተደራሽ ኤፕሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግርማ ገዳ በተደራሽ ቤት ስላሉ ውጣዊ አሰራሮች እና አባላት ሊስተናገዱበት ስለሚገቡ መንገዱች በግፅ ስልጠና ሰተዋል፡፡ በእለቱ ስለቁጠናና ብድር አያያዝ ሰፊ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በሰልጣኞች በኩል ጥያቄ በማንሳት ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በስልጠናው የመጨረሻ ቀን ላይ የተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ/ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ታመነ አባላትን በማሳተፍ እንዴት ባለመልኩ በህብረት መስራት እንደሚቻል ሰፊ ገላፃ ሰተዋል ፡፡ ነባር ቅርጫፎችም በምን መልኩ አባላትን ሲያሳትፉ እንደነበር ተሞክሮአቸውን አጋርተዋል ፡፡ መስተመጨረሻም ከወለድ ነፃ የፋይናስ አገልግሎት እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል እንዲሁም አባላት ለምን አገልግሎት መጠቀም እንደሚችሉ ከወለድ ነፃ የፋይናስ አገልግሎት ባለሙያ በሆኑት በአቶ በኢብራሂም እስማኤል ለሃላፊፎቹ ገለፃ ተደርጎ ስልጠናው ተጠናቁዋል ፡፡