Loading…

ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስ/ማ በሴንትራል አሜሪካ ፓናማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የICA ግሎባል ኮንፍረንስ ላይ ተሳተፈ ፡፡

September 24, 2026

የተደራሽ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ታመነ ተደራሽን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡በዚህ ኮንፍረንስ የህብረት ስራ መሪዎች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣የተለያዩ ሃገራት ሚኒስትሮች የተሳተፉበት ሲሆን ህብረት ስራ ማህበራት ሊጠቅሙ የሚችሉ የተለያዩ ጠንከር ያሉ ሃሳቦች ተነስተውበታል፡፡ በህብረት ስራ ማህበርት መካከል የተለያዩ የፓናል ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ ህብረትስራ ማህበራት በአለማቀፍ ደረጃ ምን ላይ እንደሚገኙ እና በቀጣይ ምን ላይ በማተኮር መስራት እንደሚገባም በውይይቱ ተነስቷል፡፡ የተለያዩ ችግሮች ያገጠሟቸው ህብረት ስራ ማህበራት በምን መልኩ ችግራቸውን መቅረፍ እንደቻሉ ልምዳቸውን አጋርተዋል፡፡ ይህ ኮንፍረስ በአለም አቀፍ ደረጃ ባሉ ህብረት ስራ ምህበራት መካከል ጥሩ ግንኙነት ከመፍጠሩ ባሻገር ህብረት ሥራ ማህበራት ሰላማዊ፣ አካታች፣ ዘላቂ እና የተረጋጋጠ የፋይናስ አቅም ያላቸው ማህበረሰቦችን በመገንባት ረገድ ያላቸውን ሚና ለመዳሰስ፣ ልምድና እውቀት ለመለዋወጥ እንዲሁም በህብረት ሥራ ዘርፍ ላይ የሚነሱ ጉዳዮችን ለመወያየት ዓለም አቀፍ መድረክ ፈጥሯል።

ተደራሽ የአለምአቀፍ ህ/ስ/ማህራት ጥምረት (ICA) አባል እንደመሆኑ መጠን በኢትዮጵያና አፍሪካ ያለውን ተቀባይነት በማሳደግ አለማቀፋዊ ግንኙነት እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ይህ ተሳትፎ ተደራሽ ያለውን አቅም ለማሳደግ እና ያለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ወደሃገር ውስጥ ለማስገባት ምን ያህል ጥረት እያደረገ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ዋና ስራ አስኪያጁ ከኮንፍረንሱ ቆይታ በኀላ ወደሃገራቸው ሲመለሱ በተደራሽ ዋና ቢሮ የእንኳን ደና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡