Loading…

ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ በቡራዩ ከተማ የሚገኘው ቅርንጫፉ ለአዲስ እና ነባር አባላቱ ገለፃ አደረገ፡፡

September 28, 2026

ገለፃው ያደረጉት ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ታመነ ናቸው፡፡ዋና ስራ አሲያጁ ስለህብረት ስራ መርህ፣ ስለ ተደራሽ አመሰራረት ስለተከናወኑ ተግባራት እና ሊሰሩ ስለታቀዱ ስራዎች ገለፃ ተደርጓል፡፡ በመረሃ ግብሩ ላይ ለአባላቱ በህብረት ስረ ማህበሩ ስር እንዴት መንቀሳቀስ እንደሚቻል እና በምን መልኩ የፋይናስ አቅምን ማጠናከር እንደሚቻል ሰፊ ገለፃ ተደርጎበታል፡፡ በስልጠናው ላይ የገፈርሳ ቡራዩ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ሙለታ ተክሌ የተደራሽ ምዕራብ ዲስትሪክት ዋና ስራ አሲኪያጅ አቶ ሚልኪያስ ሃብቴ የቡራዩ ቅርጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ቶላ የዲስትሪክት እና የቅርፍ ሰራተኞች እንዲሁም የተደራሽ ነባር እና አዲስ አባላት ተገኝተዋል፡፡ የገፈርሳ ቡራዩ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ሙለታ ተደራሽ በቡራዩ ከተማ ቅርንጫፍ ስላለው መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ አስተዳዳሪው አያይዘውም ህብረት ስራ ማህበራት የማህበረሰብን እድገት በማረጋገጥ በኩል እና አስተማማኝ የሆነ የፋይናስ አቅርቦት እንዲኖር ከማስቻል አንፃር የሚኖራቸው አስተዋፆ ቀላል የሚባል ተናግረዋል ፡፡ በቀጣይም ለተደራሽ እድገት በጋር እንደሚሰሩ አያይዘው ገልፀዋል፡፡ ነባር እና አዲስ አባላት በተደራሽ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያላቸውን ጥያቄዎች ለዋና ስራ አስኪያጁ ያነሱ ሲሆን ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡ ነባር አባለት ተደራሽ እየሰጠ ባለው አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይም ከተደራሽ ጋር ለመስራት እና በድጋሚ የመበደር እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል ፡፡