October 16, 2026
በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ እየተካሄደ ባለው በዚህ ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ጌትነት ታደሰ ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናት እንዲሁም የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ፡፡ የተለያዩ ህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒየኖች የተሳተፉበት ይህ ኤክስፖ በማህበራት በኩል የተሻለ ትስስር ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል ፡፡ ተደራሽ በቦታው በመገኘት ለተሳታፊዎቹ በሚሰጠውን አገልግሎት ላይ ገለጻ እያደረገ ይገኛል፡፡
ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ከተመሰረተ 9 አመት የሞላው ሲሆን ከ33,000 በላይ አባላት አሉት፡፡ እንደስሙ ተደራሽ ለመሆን 45 ቅርጫፎችን ከፍቶ ለአባላቱ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡