November 12, 2026
Finfinnee,onkoloolessa 29,2019 Waldaan Hojii Gamtaa Qusannaa fi Liqii Tadarraash miseensota isaaf tajaajila fooyya’aa fi saffisaa kennuu kan dandeessisan mariiwwan adda addaa cimsuun itti fufeera. Haaluma kanaan, dameen laga xaafoo miseensota waldaa isaa waliin marii gaggeesseera. Kaayyoon marii kanaa tajaajiloota Tadarraash miseensota isaaf kennu caalaatti ifa gochuu, aadaa qusannaa guddisuu, sirna liqii kennuu fi liqii deebisuu, akkasumas daangaa liqii fooyya’eefi hojimaata haaraa miseensotaaf beeksisuudha. Marii kana irratti hundeessaafi hojii geggeessaan dhaabbatichaa obbo alamaayyoo Taammannee ,miseensota argamaniif ibsa ballaa kennaniiru. Tadarraash fayyadamummaa miseensotaa guddisuuf hojiiwwan garaagaraa hojjechaa akka jiru ibsuun,lammiiwwan kuma 7000 oliif carraa hojii uumuus yaadachiisaniiru.
ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ በለገጣፎ ቅርንጫፍ ለሚገኙ አባላቱ ስለሕብረት ሥራ ማኅበራት ጥቅም፣ የቁጠባ አስፈላጊነትና የማኅበሩ አጠቃላይ አሠራሮች ላይ ያተኮረ የምክክርና የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ዝግጀቱን አባ ገዳዎች በምረቃ አስጀምረውታል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለማየሁ ታመነ ተደራሽ አሠራሩን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ለአባላት የሚሰጠውን አገልግሎት ማዘመኑን ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም ማኅበሩ አቅሙንና ተደራሽነቱን የበለጠ ለማስፋት በአፍሪካና በተለያዩ የዓለም ሀገራት ከሚገኙ መሰል የሕብረት ሥራ ማኅበራት (SACCOs) ጋር በትብብር እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመው የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ለአባላቱ ግልጽ አድርገዋል። በውይይቱ ወቅት ተደራሽ ባመቻቸው የብድር አገልግሎት ቁጠባን በማዳበር አባላት ሀብት ማፈራት መቻላቸውን የተገለፀ ሲሆን ማኅበሩ እስከ አሁን ከ7,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠሩም በመድረኩ ተነግሯል፡፡ በውይይቱ ወቅት አባላተ ተደራሽ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ያላቸውን የተለያዩ ጥዋቄዎች ያነሱ ሲሆነ በዋና ስራ አስኪያጁ በኩል ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡ አባላት ተደራሽ እያሳየ ባለው ሁለንተናዊ ዕድገት ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው ተሳትፏቸውን እንደሚቀጥሉም ቃል ገብተዋል፡፡በመድረኩም ከፍተኛ ተሳትፎ ላደረጉ አባላት እውቅና ተሰቷል ፡፡መድረኩ የአባላትን ግንዛቤ ከማሳደጉም በላይ አዳዲስ አባላትን ወደ ማኅበሩ ለማፍራት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።