November 14, 2026
ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ የአባላቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግና የስራ ዕድል ለመፍጠር እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አጠናክሮ በመቀጠል፣ በደምቢ ዶሎ ቅርንጫፍ ለሚገኙ አባላቱ 18 የኤሌክትሪክ ባጃጆችን በብድር መልክ ገዝቶ አስረከበ።
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የደምቢ ዶሎ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ላቴራ ጎሹ እንደገለጹት፣ ተቋሙ አባላቱ ከቁጠባ ባለፈ በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲያሻሽሉ በርካታ አመቺ የብድር አማራጮችን እያቀረበ ይገኛል። ይህ የባጃጅ ርክክብም አባላቱ የራሳቸውን የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩና የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያግዙ ታስቦ የተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።
ባጃጆቹን የተረከቡ አባላት በበኩላቸው፣ ተደራሽ ቁጠባና ብድር ባመቻቸላቸው ቀልጣፋና ፍትሃዊ የብድር አገልግሎት የራሳቸው ንብረት ባለቤት በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። ቀደም ሲል በኪራይ እና በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሲሰሩ እንደነበር ያስታወሱት አባላቱ፣ ተቋሙ ላደረገላቸው ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ቅርንጫፎቹን በማስፋፋት፣ ዘመናዊና ቀልጣፋ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት የአባላቱን ህይወት የመቀየር ተልዕኮውን አጠናክሮ ቀጥሏል።