Loading…

የ2017 በጀት አመት የ17 ዙር 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፡፡

March 11, 2026

ተደራሽ የቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ  መጋቢት 7/2017 ዓ.ም የ2017 በጀት አመት የ17 ዙር 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በራስ አምባ ሆቴል ምዕላት ጉባኤው በተሟላበት በስኬት አካሂዷል ።
  የ2017 በጀት አመት የ 6 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚው በሆኑት  በአቶ አለማየው ታመነ የቀረበ ሲሆን  የ2016 በጀት አመት የኦዲት ሪፖርት  በአራዳ ክ/ከ የኦዲትቡድን ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በሆላ ፀድቋል ፡፡ በተጨማሪም በዚሁ በጀት አመት  የተገኘ ትርፍ በጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች በሙሉ ድምፅ ተወስኖ የትርፍ ክፍፍሉ ወደ እጣ ዞሮ የተደራሽ የስኬት ጉዞ ያማረ እንዲሆን በማሰብ ውሳኔ ሰጥተዋል ፡፡ በማስከተልም የተለያዩ የውስጥ ደንቦች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡
መበጨረሻም የተጓደሉ የስራ አመራር ኮሚቲዎች በምርጫ በአዲስ አመራሮች እንዲሟሉ ተደርጓል፡፡ በጉባኤው ተደራሽ ወደ ፌደራል ለማደግ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ በአባል ጥያቄ ቀርቦ ከአመራሮች ምላሽ የተሰጠበት ሲሆን በምላሹም ሂደቱ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ እና በቀጣይ እንደሚሳካ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
በጉባኤው ለተሳተፉ ለጠቅላላጉባኤ ተወካዮች ፤አመራሮች በዚህ ግማሽ አመት ተደራሽ ያከናወነውን የልምድ ልውውጥ እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኩል ያሳካውን ለወጥ በመረጃ በማስደገፍ በዋና ስራ አስፈፃሚው የቀረበ ሲሆን አባላቱም የቀረበላቸውን ሪፖርት ከተመለከቱ በኋላ በተደረሽ ላይ ያላቸውን እምነትና የወደፊት ተስፋ መልካም እንደሚሆን ከወዲሁ ገልፀዋል ፡፡

Tederash Assistant

Always Online