Loading…

ለኃላፊዎች፣ለኮሚቴዎች እና ለሰራተኞች የተሰጠ ስልጠና። ተደራሽ ሚዲያና ኮምኒኬሽን

March 11, 2026

ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ  ከትናት ጀምሮ እየሰጠ የሚገኘውን በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በስራ ስነምግባር ፣ በአቅም ግንባታ እና በቡድን ስራ ላይ እየሰጠ ያለው ስልጠና በዛሬው ዕለት ቀጥሎ ውሏል።
በዛሬው እለት ስልጠናውን የወሰዱት  ከዋና ቢሮ እና  ከተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ማእከላት የተወጣጡ የተደራሽ ሰራተኞች ናቸው።
ስልጠናውን የሰጡት የተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ታመነ ናቸው። በዛሬው ስልጠና የተሳካ እና የደንበኞችን ፍላጎት ያሟላ አገልግሎት እንዴት መስጠት እንደሚቻል አቶ አለማየሁ በተብራራ መልኩ ለሰራተኛው ገለፃ አድርገዋል። በዚህ ሀሳብ ዙሪያም ከአመራሮች እና ከሰራተኞች የተለያዩ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን አቶ አለማየሁ ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ማብራሪያ ና ምላሽ ሰተውበታል።
ከዚህ በተጨማሪም በስልጠናው  ውስጥ አገልግሎት ሰጪ የሚባሉ አካላትን ማለትም ተቋም  ፣ በተቋም ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች እና ተገልጋይ ያላቸው ሚና ምን ሊሆን እንደሚገባ በዝርዝር ስልጠና ተሰቶበታል።
በዛሬው ስልጠና በተቋም ውስጥ ሊኖር ስለሚገባ የስራ ስነምግባር በስፋት ተቃኝቷል።
ማንኛውም የተቋም ሰራተኛ የስራ ስነምግባር የሚባሉትን ሰዓት አክባሪነት፣ ተገቢ ባህሪ ማሳየት፣ በቡድን ስራ ማመን፣ የስራ ቦታን የሚመጥን አለባበስ መጠቀም፣ ለስራ በተሰማራንበት ቦታ አውንታዊ አመለካከት መኖር ፣ ምርታማነትን ማሳደግ፣ በቂ ክህሎት ይዞ መገኘት እና የመሳሰሉት ስነምግባራት ሰራተኛው ተላብሶ መገኘት እንደሚገባውም አቶ አለማየሁ በስልጠናው ወቅት ገልፀዋል።
ከላይ የተጠቀሱትን የስራ ስነምግባሮች ተላብሶ መገኘት ተቋምን ከማሳደግ ባሻገር እንዴት በሰራተኛ የግል ሂወት ላይ ጭምር የሚያመጣውን  ለውጥ አክለው ገልፀዋል። ስልጠናው በነገው እለትም ቀጥሎ የሚውል ይሆናል።

Tederash Assistant

Always Online