ከSOS ጋር በመተባርበር የተሰጠ ስልጠና
ተደራሽ ሚዲያና ኮምኒኬሽን
March 11, 2026
ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ከሚያዚያ 2/2017 ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት ለኃላፊዎች ፣ ለኮሚቴዎች እና ለሰራተኞች ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል። በዛሬው እለት በተከናውነው ስልጠና የተደራሽ አጋር የሆነው SOS Ethipoia የተገኘ ሲሆን በተወካኙ በኩል ለተደራሽ ኃላፊዎች፣ኮሚቴዎች እና ሰራተኞች ስልጠና ተሰቷል። ስልጠናውን የሰጡት አቶ ሚኪያስ አለማየሁ ሲሆኑ በደምበኛ አያያዝ ዙሪያ ሰፋ ያለ ሀሳብ አንስተዋል። ተደራሽ እንደ ተቋም ትኩረት አድርጎ ሊሰራበት የሚገባው ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰቶ ሊሰራ እንደሚገባም ጨምረው ገልፀዋል።
በደምበኛ አገልግሎት ልቆ መገኘት በአንድ ተቋም ውስጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን የገለፁት አቶ ሚኪያስ ከደንበኞች ጋር መደረግ ስለሚኖርበት ተግባቦት ሰፉ ባለመልኩ ስልጠና ሰተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ታማኝ ደምበኛ ማፍራት ስለሚቻልባቸው መንገዶች በስፋት ስልጠና ተሰቶበታል። ይህንንም ለማሳካት ደንበኛው አገኘዋለው ብሎ ከሚያስበው አገልግሎት በላይ ልቆ መገኘት እንዲሁም ቋሚ እና ቀጣይነት ያለውን አሰራር መገነንባት አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል። ተቋማት ከደንበኛ አያያዝ በተጨማሪ የተቋሙ ሰራተኞች ላይ አተኩረው ሊሰሩ እንደሚገባም በስፋት ተነስቷል። በተለይ ለሰራተኞቻቸው በተለያዩ ጊዜያት ስልጠና መስጠትና የኔነት ስሜት በሰራተኛው ውስጥ ማስረፅ እንደሚጠበቅባቸው ተጠቅሷል።
በዛሬው ዕለት ከሰዓት በነበረው መርሀግብር የተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ታመነ ። ስለ ህብረት ስራ ማህበራት አላማ እና መርሆች በስፋት በማንሳት ለሰራተኛው አብራርተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የቁጠባ ጥቅምና ዘመናዊ የቁጠባ ባህሪያት ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰቶ ስልጠናው ጠተናቋል።