ትንሽ ቆጥቦ ትልቅ መሆን እንደሚቻልና ጠንክሮ ለሚሰራ ሰው ብድር ትልቅ የአድገት መሰላል መሆኑን በተግባር አረጋግጠዋል።
የተደራሽ የብድርና ቁጠባ ማህበር አባላት የሆኑት እነ አቶ ታደሰ ዳመና እና አቶ ወንድማገኝ ማሞ፣ ቀደም ሲል የነበራቸው የመኪና ባለቤት የመሆን ህልም በተደራሽ አማካኝነት እውን ሆኖላቸዋል። አቶ ታደሰ ስለ ማህበሩ መረጃውን ካገኙ በኋላ በፒያሳ በሚገኘው ዋና ቢሮ በመሄድ ለስድስት ወራት አምስት ፐርሰንት (5%) በመቆጠብ የግል መኪና ባለቤት መሆን ችለዋል። በተመሳሳይ መልኩ አቶ ወንድማገኝ ማሞ ስለ ተደራሽ አገልግሎት በማህበራዊ ሚዲያ ሰምተው ሃያ ፐርሰንት (20%) በመቆጠብ የጭነት ተሽከርካሪ (FSR) ባለቤት በመሆን ስራቸውን ለማሳለጥ በቅተዋል። በተጨማሪም ማህበሩ በግብርናው ዘርፍ ለሚሰማሩ አባላቱ የሶሊስ (Solis) ትራክተር ብድር በማመቻቸት የገበሬውንና የባለሀብቱን ህይወት እየቀየረ ይገኛል። እነዚህ አባላት እንደሚመሰክሩት፣ ትንሽ ቆጥቦ ትልቅ መሆን እንደሚቻልና ጠንክሮ ለሚሰራ ሰው ብድር ትልቅ የአድገት መሰላል መሆኑን በተግባር አረጋግጠዋል።